ሳንቼዝ ወደ ማን ዩናይትድ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሷል

0
2207
Sponsored

✔አሌክሲስ ሳንቼዝ ወደ ማን ዩናይትድ የሚያደርገው ዝውውር ዛሬ ምሽት  እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡ቺሊያዊው ኮከብ በአርሰናል ደስተኛ አለመሆኑን በተደጋጋሚ ሜዳ ውስጥ ተቃውሞውን በመግለፁ በቡድን አጋሮቹ  ፊት ተነስቷል፡፡

 

Sponsored

ውሉ በመጪው ክረምት የሚጠናቀቀው ሳንቼዝ ከባለፈው አመት ጀምሮ በኤምሬትስ ውሉን እንዲያራዝም በአርሰናል የቦርድ አባላት ቢፈለግም እሱ ግን እንቢታን መርጧል፡፡በቦስማን ህግ መሰረት ውሉን ለማራዘም ፈቃደኛ ካልሆነ ክረምት ላይ ወደ ፈለገበት ክለብ የመሄድ መብት በነፃ የመሄድ መብት ስላለው መድፈኞቹ በዚህ የጥር ወር የዝውውር መስኮት መሸጥ የግድ ይላቸዋል፡፡

 

ከሀገረ ቺሊ ዛሬ የወጡ መረጃዎች እንዲሁም በርካታ የእንግሊዝ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ይህ ዝውውር የመሳካቱ ነገር እሙን ነው ማምሻውንም ተጠናቆ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡

 

ሳንቼዝ ቀያይ ሰይጣኖቹን የሚቀላቀል ከሆነ በታሪክ የመጀመሪያ ቺሊያዊ የማን ዩናይትድ ማሊያን የለበሰ ተጨዋች ይሆናል፡፡ታሪካዊውን ሰባት ቁጥር መለያም እንደሚለብስ ይጠበቃል፡

Sponsored

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here