“ሳንቼዝ ወደ ማን ዩናይትድ በመሄድህ እንኳን ደስ አለህ” ፔፕ ጋርዲዮላ

1
3470
Sponsored

“ሳንቼዝ ወደ ማን ዩናይትድ በመሄድህ እንኳን ደስ አለህ” ፔፕ ጋርዲዮላ

 

Sponsored

 

❀ስፔናዊው የቲካ ታካ ማስተር የውሃ ሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ወደ ማን ዩናይትድ ለመቀላቀል ከጫፍ ለደረሰው አሌክሲስ ሳንቼዝ ‘መልካም ዕድል’ ተመኝቷል፡፡

ማን ሲቲ ባሳለፍነው አመት ቺሊያዊውን ኢንተርናሽናል ወደ ኤቲሀድ ለማምጣት እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ጥረት ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

አርባ ሰባተኛ አመት ልደቱን ትናንት ያከበረው የመልካም እግር ኳስ አቀንቃኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ዛሬ ለጋዜጠኞች ከኒውካስትል ጋር ስላለባቸው ጨዋታ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲህ በማለት ተናግሯል

 

“እኔ ስለ ሂሳብ እና ቁጥሮች የማስብ ሰው አይደለሁም ፡፡አሁን የማውቀው እሱ የአርሰናል ተጨዋች መሆኑን ነው

 

ወደ ማንቸስተር ዩናይትድ ለመዘዋወር መንገድ ላይ እንደሆነም አውቃለው፡፡ለሁለቱም አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ማለት ፈልጋለው፡፡ተጨዋቾች የመምረጥ እድል ሲሰጣቸው ወዴት መሄድ እንዳለባቸው ይወስናሉ፡፡መልካም ዕድል!

 

ተጨዋቾች እና ወኪሎቻቸው ለራሳቸው  ጥሩ ነው ብለው የሚያስቡትን ይመርጣሉ ፡፡

ለአሌክሲስ ያለኝ ግምት አሁንም ተመሳሳይ ነው፡፡ከሱ ጋር በባርሴሎና መስራቴ ሁሌም ያስደስተኛል፡፡እሱ አሁን ወደ ሌላ ክለብ ለመሄድ ወስኗል ስለዚህ እኔ መልካም ዕድል እመኝለታለው፡፡”

 

❀ፔፕ ጋርዲዮላ ይህንን ማለቱ ሲቲ በሳንቼዝ ጉዳይ ተስፋ መቁረጡን ያሳያል፡፡ቺሊያዊው ኮከብ ነገ አርሰናል ከ ክሪስታል ፓላስ በሚያደርገው ጨዋታ ለመጨረሻ ጊዜ የመድፈኞቹን ማልያ እንደሚለብስ ይታወቃል፡፡

Sponsored

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here