እለተ ሰንበት ምሽት የወጡ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

1
2743
Sponsored

✔በመጪው ክረምት ውሉ የሚጠናቀቀው የመድፈኞቹ አጥቂ አሌክሲስ ሳንቼዝ በጥር ወር የዝውውር መስኮት  ኤምሬትስን ከሚለቁ ተጨዋቾች ግንባር ቀደሙ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ቺሊያዊው የግብ አነፍናፊን ለማስፈረም ሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች እየተፎካከሩ ሲሆን ሊቨርፑልም እዚህ ዝውውር ላይ አለሁበት እያለ ነው፡፡የጆዜ ሞሪንሆው ማን ዩናይትድ በዋናነት የሚፈልገው ግን ሜሱት ኦዚልን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

 

Sponsored

✔ፌሊፔ ኩቲንሆን በ€160M ለካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የሸጡት ቀያዮቹ ሊቨርፑሎች የብራዚላዊውን የጨዋታ ቀማሪ ቦታ ለመተካት ገበያው ላይ እየኳተኑ ነው፡፡ በዋናነት ከሚፈልጓቸው ተጨዋቾች ውስጥ አንዱ ደግሞ የ22 አመቱ ፖርቹጋላዊ የስፖርቲንግ ሊዝበን የክንፍ አጥቂ ጌልሰን ማርቲንስ ይገኝበታል፡፡

 

✔እንደ ማድሪድ ዘመሙ ጋዜጣ Marca ሀተታ  ምንም እንኳን በዚህ ሲዝን ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ቢሆንም የፍሎረንቲኖ ፔሬዝ አስተዳደር ዚነዲን ዚዳንን ከሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነቱ መሻር አይፈልግም ፡፡ ፈረንሳዊው የክለቡ ሌጀንድ የነበረው ዚዳን ሻምፒዮንስ ሊግን በተከታታይ አመት በማሸነፍ ስሙን በወርቅ ብዕር ማስፈሩ ይታወሳል፡፡

 

✔አመቱ ከመጀመሩ በፊት ቀውስ ውስጥ ከነበሩ ክለቦች አንዱ ነበር ባርሴሎና!

ሆኖም ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆኖ የካታላኑ ክለብ ውጤታማ እየሆነ ይገኛል፡፡አርዳ ቱራንን ወደ ሀገሩ ቱርክ የሸኙት ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ ሌሎች ተጨማሪ አምስት ተጨዋቾች ከክለቡ እንዲለቁ ይፈልጋሉ፡፡

 

✔በከባዱ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ አስገራሚ ግስጋሴ ላይ የሚገኘው የፔፕ ጋርዲዮላው ማን ሲቲ በዚህ በጥር ወር የዝውውር መስኮት  ተጨዋቾችን በማስፈረም ይበልጥ ስኳዱን ማስፋት ይፈልጋል፡፡ለዚህም ይረዳው ዘንድ የ18 አመቱን የፓሪሰን ጀርሜን  ታዳጊ አማካይ ቦባካሪ ሴማሬ ኢላማ አድርጎ እየሰራ ነው፡፡

 

✔አዲሱ የባርሴሎና ፈራሚ ዬሪ ሚና ከደጋፊዎቹ ጋር ሲተዋወቅ በባዶ እግሩ ወደ ኑ ካምፕ በመግባት ብዙዎችን አስገርሟል ፡፡የ23 አመቱ ኮሎምቢያዊ ተከላካይ ይህንን ያደረገው ከመጽሐፉ ቅዱስ ላይ ባነበበው ስንኝ እንደሆነም ተናግሯል ፡፡

 

✔ በአሰልጣኝ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ ስር ብቃታቸውን ካደበሩ ተጨዋቾች መሀከል የሆኑት ሀሪ ኬን፣ኤሪክሰን እና ሰን ሁንግ ሚን ይጠቀሳሉ፡፡የዳኒ ሌቪ አስተዳደር በነዚህ ተጨዋቾች ዘንድ የዝውውር ጥያቄ መብዛቱን ተከትሎ ውላቸውን የሚያራዝም ኮንትራት አቅርቦላቸዋል፡፡

 

  • ✔ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ብሎም በአለም ደረጃ ካሉ ምርጥ ግብ ጠባቂዎች አንዱ ዴቪድ ዴሄያ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ሪያል ማድሪድን ጨምሮ በበርካታ የአለም ታላላቅ ክለቦች የሚፈለገውን ስፓኒያርድ በኦልድ ትራፎርድ ለማቆየት ቀያይ ሰይጣኖቹ £300,000 ሳምንታዊ ደሞዝ አቅርበውለታል፡፡
Sponsored

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here