የእለተ ሀሙስ ምሽት አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

2
3663
Sponsored

የዝውውር ዜናዎቹን እነሆ

❀በጎል ድርቅ ለተከታታይ ጨዋታዎች የተመቱት ሰማያዊዎቹ በዝውውር መስኮቱ የአጥቂ መስመራቸው ማጠናከር አለባቸው የሚለው የብዙዎች ሀሳብ ነው፡፡

Sponsored

ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ ጣሊያናዊው የታክቲክ ልሂቅ አንቶኒዮ ኮንቴ በጁቬንቱስ ሳሉ አብረውት የሰሩትን በአሁን ሰዓት ቶተንሀም የሚገኘውን ቁመተ መለሎ አጥቂ ፈርናንዶ ሎሬንቴ ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት እየሰሩ ነው፡፡

❀በዘንድሮው አመት ከሚገባው በላይ በመውረድ በላሊጋው ባልተለመደ መልኩ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሎስብላንኮስ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተሰነዘረባቸው ነው፡፡እንደ ማድሪድ ዘመሙ ጋዜጣ ማርካ ዘገባ  ለተጨዋቾች ዝውውር ያልተጠበቀ ገንዘብ የማውጣት ልምድ ያላቸው ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ኔይማር፣ሀዛርድ እና ሌቫንዶልስኪን እቅድ አድርገዋል ፡፡

❀ የቀድሞው የማን ዩናይትድ ተጨዋች ፊል ኔቭል ከbbc radio 5 ጋር ባደረገው ቆይታ ስለ አርሜንያዊው ሄንሪክ ሚኪታሪያን ሲናገር ወደ አርሰናል ቢሄድ ለእግር ኳስ ህይወቱ ጥሩ እንደሆነ እና ጥሩ እንቅስቃሴ ያደርጋል ብሎ እንደሚያስብ ተናግሯል ፡፡

❀ የኒውካስትሉ አሰልጣኝ ራፋ ቤኒቴዝ አሁን ባላቸው ስኳድ ደስተኛ ስላልሆኑ ገንዘብ በማውጣት ለሚታሙት የክለቡ ባለ ሀብት ማይክ አሽሊ  ገንዘብ እንዲመድቡላቸው ጠይቀዋል ፡፡

❀ ሊቨርፑል የሻልኩን ድንቅ አማካይ ሊዮ ኮርቴዝካ  የማዘዋወር ከፍተኛ ፍላጎት ቢኖረውም የቡንደስሊጋው ተጨዋቾች በማደን ልምድ ያለው የባቫሪያው ባየርን ሙኒክ ራስምታት ሆኖበታል፡፡

❀እንደ ጣሊያኑ ጋዜጣ tuttosport ዘገባ ጁቬንቱስ የ22 አመቱን ስፓንያርድ የመድፈኞቹ የቀኝ መስመር ተከላካይ ሄክቶር ቤለሪን በጥር ወር የዝውውር መስኮት ማስፈረም ይፈልጋል፡፡አሮጊቷ ቤለሪንን ከ2014 ጀምሮ ፈላጊው መሆኗ ይታወሳል፡፡

❀በተደጋጋሚ የልቀቁኝ ጥያቄ ያቀረበውን ፔር ኤምሪክ ኦባማያንግ ለመሸኘት ቢጫ ሰርጓጆቹ ቦሩሲያ ዶርትሙንዶች ወስነዋል፡፡ጋቦናዊው ኢንተርናሽናል በአርሰናል እና ቼልሲ በጥብቅ የሚፈለግ ሲሆን ዶርትመንዶች በምትኩ ሚቺ ባትሹዋይን አስበዋል፡፡

❀በኤምሬትስ ያለው ውል ሊጠናቀቅ ስድስት ወር የቀረው አሌክሲስ ሳንቼዝ ማን ዩናይትድን ለመቀላቀል ከጫፍ ደርሷል ፡፡ሳንቼዝ ዛሬ የማን ዩናይትድ የልምምድ ቦታ ካሪንግተን ተገኝቶ የህክምና ምርመራ እንዳደረገ በርካታ ሚዲያዎች የዘገቡ ሲሆን ሰባት ቁጥር ማሊያም በስሙ ታትሞ እየተቸበቸበ ነው፡፡

Sponsored

2 COMMENTS

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here