የእለተ ቅዳሜ አዳዲስ የዝውውር ዜናዎች

0
1880
Sponsored

በዘንድሮው አመት ከባድ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሪያል ማድሪድ አሰልጣኙን ዚነዲን ዚዳን ሊያሰናብት እንደሚችል እየተዘገበ ነው፡፡አሰልጣኞችን የማሰናበት አባዜ ያለባቸው ፕሬዝደንቱ ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ እስካሁን ለዚዳን ካላቸው ክብር እና በተጨዋችነት ዘመኑ በሰራው ገድል ምክንያት እስካሁን አቆይተውታል፡፡እንደ Mail ዘገባ ከሆነ ሎስብላንኮስ በቀጣዩ አመት የአሰልጣኝ ቅያሪ በማድረግ አርጀንቲናዊውን የስፐርስ አለቃ ማውሩሲዮ ፖቼቲንሆ መቅጠር ይሻሉ፡፡

 

Sponsored

 

ማንቸስተር ሲቲ በበርካታ የአውሮፓ ክለቦች በጥብቅ ሲፈለግ የነበረውን ፈረንሳዊ የአትሌቲክ ቢልባኦ የመሀል ተከላካይ አይሜሪክ ላፖርቴ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡፡በዘንድሮው የውድድር ዘመን አስደናቂ ግስጋሴ በፕሪሚየር ሊጉ እያሳለፉ የሚገኙት ውሃ ሰማያዊዎቹ ይበልጥ ስኳዳቸውን በማስፋት ላይ ይገኛሉ፡፡

 

ባልተለመደ መልኩ በሊጉ አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ሪያል ማድሪድ ለጥቂት አመታት ትቶት የነበረውን ‘ጋላክቲኮ ‘ ፖሊሲ በቀጣዩ አመት ይጀምራል፡፡ዋነኛ እቅዶቹ ደግሞ ቤልጄሚያዊው የሰማያዊዎቹ ኮከብ ኤድን ሀዛርድ፣እንግሊዛዊው የስፐርስ  ጨራሽ ስፔሻሊስት ሀሪ ኬን እና ድንቁ የማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ሀሪ ኬን ናቸው፡፡

 

የጌጌም ፕሬሲንጉ አቀንቃኙ አሰልጣኝ ጀርደን ክሎፕ በተደጋጋሚ ጉዳት የእግር ኳስ ህይወቱ የላሸቀውን ዳኔል ስተሪጅን በቋሚነት ከዚ በኃላ አሰልፈዋለው ብለው ቃል መግባት እንደማይችሉ ተናግረዋል ፡፡

 

ቁመተ መለሎ የሆኑ አጥቂዎችን በማሰስ ላይ የሚገኘው ቼልሲ የቀድሞውን የማን ሲቲ እና አሁን ሮማ የሚገኘውን ኤዲን ዜኮ ለማስፈረም የሚያደርገው ጥረት የማይሳካ ከሆነ ወደ ሌላ ተጨዋች አይኑን ያዞራል፡፡

 

አንቶኒዮ ኮንቴ ከጋርዲያን ጋር ባደረጉት ቆይታ በስታንፎርድ ብሪጅ ለብዙ አመታት ማሰልጠን የማይታሰብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ጣሊያናዊው የታክቲክ ኤክስፐርት ባሳለፍነው አመት ገና በመጀመሪያ አመታቸው ፕሪሚየር ሊጉን በማንሳት ከብዙዎች አንቱታን ያገኙ ቢሆንም በዘንድሮው አመት ግን ከተሰጣቸው ግምት አንፃር ዝቅ ብለዋል፡፡

 

ትናንት በኤፍ ኤ ካፕ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ዮቪልን 4 ለ 0 በረታበት ጨዋታ አሌክሲስ ሳንቼዝ የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል ፡፡ፖርቹጋላዊው የቀያይ ሰይጣኖቹ አለቃ ጆዜ ሞሪንሆም በቺሊያዊው ኢንተርናሽናል አቋም ደስተኛ መሆናቸውን ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል ፡፡

Sponsored

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here